“እንጅባራ መምህራን ኮሌጅ ላለፍት አመታት በአዊኛ በቋንቋ የሚያስተምሩ መምህራን እጥረት በመፍታት ረገድ እያበረከተ ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው።”

በዛሬው እለት የእንጅባራ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ለ12ዙር 761 በተለያዩ የትምህርት ክፍል ያስተማራቸውን ተማሪዎች አስመርቋል ።በዕለቱ በክብር እንግድነት የተገኙት የብሄ/አስ ትምህርት መምሪያ ሀላፊ አቶ ሙሉቀን መኮነን እንደተናገሩት የእንጅባራ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ላለፍት አመታት በአዊኛ በቋንቋ የሚያስተምሩ መምህራን እጥረት በመፍታት ረገድ እያበረከተ ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው ብለዋል።
ተመራቂዎች ተወዳዳሪ ሁነው ለሀገሪቱ ሁለንተናዊ እድገት የበኩላቸውን እንዲወጡ አንባቢና እና ተመራማሪ እንዲሆኑም መልዕክት አስተላልፈዋል ።
ተመራቂ እጩ መምህራን በሠጡት አስተያየት በኮሌጁ ቆይታቸው ባገኙት እውቀት እና ክህሎት ኩረጃን የሚጠየፍ ትውልድ በመቅረጽ የትምህርት ጥራት እንዲረጋገጥ የበኩላቸውን ለመወጣት እንደሚሰሩ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል ።
በላይነሽ አበበ