አሁን ላይ መንግስት በዘረጋው የመምህራን ትምህርት ኮሌጆች የደረጃ ሽግግር እንጅባራ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ከዲፕሎማ ወደ ዲግሪ መርሃ ግብር ማደግ ችሏል።
ህዳር 11/2015(አዊ ኮሙኑኬሽን) ዛሬ የኮሌጁ ይፋዊ የዲግሪ ፕሮግራም ማስጀመሪያ መርሃ ግብርና የሴት ተማሪዎች ዶርሚታሪ ማስመረቅ ፕሮግራም ተከናውኗል።
በፕሮግራሙ የአብክመ ትምህርት ቢሮ ም/ሀላፊ አቶ መኳንንት አደመ፣የአዊ ብሄ/አስ ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንግዳ ዳኛው ፣የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጋርዳቸው ወርቁ ፣ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የሀገር ሽማግሌዎችን ጨምሮ ኮሌጁ ያለበትን ደረጃ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
በበላይነሽ አበበ
